Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በክልሉ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ ነው አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፡፡
‎‎በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “እውቅና ለተሻለ ገቢ አሰባሰብ” በሚል መሪ ቃል 5ኛው ዙር የታክስ ንቅናቄ እና የግብር ከፋዮች የዕውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ በየዓመቱ በከፍተኛ መጠን እያደገ መጥቷል፡፡
በክልሉ በተያዘው 2019 በጀት ዓመት 15 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደሥራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡
‎በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት 10 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ በክልሉ መሰብሰብ ተመላክቷል፡፡
‎የክልሉ መንግስት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለሰበሰበው ግብር የታማኝ ግብር ከፋዮች እና የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት በተካሄደ ጥናት መሰረት ክልሉ ባለው የገቢ አቅም ልክ እየተሰበሰበ አለመሆኑን ጠቁመው፤ የክልሉን የገቢ አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
የክልሉ መንግሥት በግብር አካፋፈል ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት እና የገቢ አቅምን በማሳደግ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
‎በመርሐ ግብሩ በክልሉ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ለታማኝ ግብር ከፋዮች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዕውቅና መሰጠቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.