Fana: At a Speed of Life!

የማንሰራራት ቀን በቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስፍራ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንሰራራት ቀን በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ስፍራ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ በቱሪዝም፤ ግብርና፤ ማዕድንና ነዳጅ፤ ውሀና ኢነርጂ፤ ትራንስፖርት እንዲሁም በከተማና መሰረተ ልማት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን፤ የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች የግንባታ ሂደቱን ጎብኝተዋል፡፡
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.