Fana: At a Speed of Life!

የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ7 ከተሞች ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ7 ከተሞች ይደረጋል አለ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር፡፡
ሊግ ካምፓኒው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጸው፤ የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ7 ከተሞች በሚገኙ ሰባት ስታዲየሞች ይካሄዳል፡፡
አዲስ አበባ ስታዲየም፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ ባህር ዳር ከተማ ስታዲየም፣ አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አባያ ካሞፓስ ስታዲየም፣ ሆሳዕና አብዬ ኤርሳሞ ስታዲየም እና ሀላባ ስታዲየም ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ናቸው።
የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የእጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም አዲሱ የውድድር ዓመት የሚጀምር ይሆናል፡፡
በእንዳልካቸው ወዳጄ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.