Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከ2ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዛሬው ዕለት ከ2ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀምሯል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) ፥ ተቋሙ በተለያዩ መልኮች ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በሪፎርም ወደ ትርፋማ ምዕራፍ ተሸጋግሯል ብለዋል።

በዚህም ትርፉን በ42 እጥፍ ማሳደግ መቻሉንና በዛሬው ዕለትም ከ2ሺ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ግንባታ በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ በአልሚዎች ትብብር የሚገነባ ሲሆን ባለስድስት ወለል ሕንፃና በቂ የመኪና ማቆሚያ፣ዘመናዊ መዝናኛ ቦታዎችን ከነሱቆቹ የያዘ ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በሱቆቹ ለልማቱ የሚነሱት 230 ነባር ተከራዮችን ጨምሮ ተጨማሪ ዜጎች እድል እንደሚፈጠርላቸውም አስረድተዋል።

ኮርፖሬሽኑ በአንድ ዓመት ውስጥ አስር ህንፃዎችን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙንና ወደ 10 ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ግንባታዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አንስተዋል።

በሌላ በኩል የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመርካቶ ያስገነባውቸን 399 ሱቆችንም በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.