ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፥ ከ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መክረናል ብለዋል።
በውይይቱ በዋና ዋና የብሪክስ ቅድመ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብር የበለጠ በሚያጠናክሩ ሂደቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል።