Fana: At a Speed of Life!

የተሾሙ ሚኒስትሮች ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል – የምክር ቤት አባላት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሾሙ ሚኒስትሮች ለህዝብ የቀረቡ ሥራዎችን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል አሉ የምክር ቤት አበላት።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
በዚህም በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔያቸውን እጩዎች አባላት ዝርዝር አቅርበው በምክር ቤቱ ፀድቋል።
የ22ቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የቀረቡ ዕጩዎችን አስመልክቶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት÷ የተሾሙ የምክር ቤት አባልት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጡ እና የሚመሩ ሊሆኑ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የተሾሙት የካቢኔ አባላት በልዩ ዕይታ የተመረጡ ናቸው ተብሎ የታመነባቸው እንደሆኑ አንስተው ነገር ግን በሥራ ዘመናቸው ለማህበረሰቡ የቀረበ ሥራን መሥራት መርህ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር እንደሆነች እና ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ከብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆና ብዙ ለውጦችን እንዳስመዘገበች ገልጸው ይህን እድገቷን ለማስቀጠል ብሎም ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ማስተካከል ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.