Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ክብርና የጀግንነት ድል የሚገለጸው ሰንደቅ ዓላማን ከፍ በማድረግ ነው – አቶ ሃይሉ አዱኛ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ክብርና የጀግንነት ድል የሚገለጸው ሰንደቅ ዓላማን ከፍ በማድረግ በመሆኑ፤ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነትና የሕዝቦች አንድነት ታላቅ መገለጫ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ፡፡

“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሃሳብ 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ ሃይሉ አዱኛ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ምልክት፣ የሀገር ማንነት መገለጫ እንዲሁም የሕዝቦችን ማንነት የሚያከብርና የሚያስተዋውቅ ዋነኛ ምልክት ነው ብለዋል።

የፖለቲካ ነፃነት፣ ወሰንና ድንበር እንዲሁም የራሳቸው ማንነት ያላቸው የዓለም ሀገራት በሙሉ ነፃነታቸውንና ማንነታቸውን የሚወክል ሰንደቅ ዓላማ እንዳላቸውና ሰንደቅ ዓላማ የሀገርን መልካም ስም ለዓለም የሚያስተዋውቅና ነፃነትን ከፍ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑንም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.