Fana: At a Speed of Life!

ሰንደቅ ዓላማችን ሉዓላዊነታችንን እና አብሮነታችንን የሚያንጸባርቅ ሕያው የታሪክ ምስክር ነው- ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችንን ክብርና የአብሮነታችንን ጽናት የሚያንጸባርቅ ሕያው የታሪክ ምስክር ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)።

ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ሰንደቅ ዓላማ የታሪክ ምስክር ብቻ ሳይሆን የዛሬ ኃላፊነትንና የነገን የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚያስታውስ ሀገራዊ አደራ ነው ብለዋል።

ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት፣ የሉዓላዊነትና የኅብረ-ብሔራዊ አንድነት የማይደበዝዝ ዓርማና በትውልዶች መካከል ያለውን የሀገር ፍቅር ድልድይ የሚያስተሳስር የጋራ ማንነት መሆኑንም አመልክተዋል።

አክለውም የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ብዝኃነትን ወደ የጋራ ጥንካሬ በመቀየር፣ መከባበርና መተማመንን በማጠናከር እንዲሁም ለዘላቂ ሰላም፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለጋራ ብልጽግና በቁርጠኝነት ለመስራት ቃል ልናድስ ይገባል ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.