Fana: At a Speed of Life!

የምክር ቤት ሥራዎችን ለማሳለጥ የሚያግዝ አማካሪ ኮሚቴ ተሰየመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ሰይሟል፡፡
ኮሚቴው የምክር ቤቱን አጀንዳ የሚቀርጽ፣ ዓመታዊ በጀት የሚያዘጋጅ፣ የሰው ኃይል፣ የፋይናንስና የንብረት አስተዳደርን የሚከታተል እንዲሁም የምክር ቤቱን ደንብ የሚተረጉምና መመሪያ የሚያወጣ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አፈ ጉባኤ አህመድ ሺዴ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ በእጩዎች የአመራረጥ ሂደት ከመንግስት ተጠሪና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አማካሪ ኮሚቴው ብዝሐነትን፣ ብቃትን፣ የሥራ ልምድን፣ በምክር ቤቱ መቀመጫ ያላቸውን የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ታሳቢ ያደረገ እንዲሁም አዲስና ነባር አባላትን ያካተተ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አንስተዋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ
2. የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ
3. በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ
4. በምክር ቤቱ ሁለት ረዳት የመንግሥት ተጠሪዎች
5. አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)
6. አቶ አብዱ ሐሰን
7. ጥላሁን አርዱኖ (ዶ/ር)
8. ካሳሁን ደለነ (ዶ/ር)
9. አቶ የሱፍ ኢብራሂም
10. አቶ ዝኑር አብዱልዋሂብ
11. ወ/ሮ ፈተና ባዩ
12. አቶ ለገሰ ላንቃሞ ሆነው ተሰይመዋል፡፡
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ የአማካሪ ኮሚቴውን አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.