Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦችን መርምሮ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ካጸደቃቸው የውሳኔ ሀሳቦች መካከል የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ይገኝበታል።

በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነትን ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መጽደቁም ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.