የመደመር መንግሥት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ መርሁ ነው – አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) – የመደመር መንግሥት የሚያከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃት መርሁ ነው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ቤተ-መንግሥት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡
አቶ አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት ፥ ፕሮጀክቱ የመደመር መንግሥትን የሥራ ከባቢን በመለወጥ ደረጃቸውን የጠበቁ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ርዕይን ማዕከል ያደረገ ነው ብለዋል።