Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ለመከላከያ ሠራዊት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡
የድጋፍ ሰልፎቹ በጎንደር፣ ሰቆጣ፣ ደብረ ታቦር፣ ወልዲያ፣ ገንዳ ውሃ እና ሌሎች ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልፈኞቹ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር አንድነትንና ሉዓላዊነትን ለማጽናት እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ለመደገፍ ያለመ ነው፡፡
በሰልፉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.