Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ አስተዳደር ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የድሬዳዋ ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት ሦስት ወራት ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቤያለሁ አለ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሙሉካ መሐመድ ፥ ከሐምሌ 1 ቀን 2018 እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ሦስት ወራት 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም የእቅዱን 86 ነጥብ 84 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ተናግረዋል።

ባለፉት ሦስት ወራት ከመንግሥት ታክስና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ766 ሚሊየን ብር በላይ ወይም ከ43 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ ለገቢው መሰብሰብ ግብር ከፋዩ ማህብረሰብ የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ በመክፈሉና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.