የውጊያ ማርሽ ቀያሪው፤ የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘመናዊው የጦርነት ስልት እና የደህንነት ሥጋት ውስጥ ፈጣን ተለዋዋጭነት፣ ትክክለኛነት እና በሁሉም መስኮች ዝግጁ መሆን የአንድን ሀገር መከላከያ ሠራዊት ጥንካሬ ይወስናሉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በየብስ፣ በአየር እና በባህር የሚሰጡትን ውስብስብ ግዳጆች በአስተማማኝ ሁኔታ መወጣት የሚያስችል ሁለንተናዊ ወታደራዊ ብቃት ገንብቷል።
የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች አዛዥ ሌ/ጄነራል ሹማ አብደታ ለህገ መንግሥቱ ታማኝ የሆነ፣ ጠላቱን የሚያስፈራ፣ ወገኑን የሚያኮራ፣ ውጊያዎችን በአጭር ጊዜ የሚጨርስ፣ ጠላቶቻችን ስጋት ውስጥ እንዲገቡ ያደረገ የመሬት ላይ ድሮን የውጊያ ማርሽ ቀያሪ የሚል ስያሜ የተሰጠው የልዩ ዘመቻ ዕዝ ነው በማለት በአንድ ወቅት ገልጸውት ነበር፡፡
የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጀግንነቱ ትናንትም የነበረ ዛሬም የቀጠለ፤ ሀገራችንን ለመድፈር የሚሞክሩትን ለመመከት እና ለማጥቃት በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡
ይህ የተቀናጀ አቅም በምሥራቅ አፍሪካ ወታደራዊ ሚዛን ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ፤ የዕዙ ኃይሎች ከተለመደው የየብስ ውጊያ ባለፈ በማንኛውም የጦርነት ምህዳር ውስጥ በበላይነት ለመንቀሳቀስ ያለውን ሙሉ ቁመና ያሳያል።
ዕዙ በአዳዲስ የጦር መሣሪያዎች፣ በዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች እና ትክክለኛ ኢላማቸውን በሚመቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የተደራጀ ነው፡፡
ሀገራዊ ሰላምን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖችን ገና ከመነሻቸው የሚያቀር ኃይል ተገንብቷል፤በዚህም ኢትዮጵያ በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ ያላትን ተሳትፎና ተደማጭነት አሳድጓል፡፡
የሀገሪቱ ወሳኝ መሰረተ ልማቶች፣ የንግድ መስመሮች እና ድንበሮች ከማንኛውም ዓይነት የጠላት ጥቃት የተጠበቁ መሆናቸውን ዋስትና ሰጥቷል፡፡
በአጠቃላይ የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ከተለመደው ወታደራዊ አወቃቀር ወጥቶ የሶስት ምህዳሮች ኃያል መሆን ችሏል።
በየብስ፣ በአየርና በባህር ላይ የገነባው አስተማማኝ ብቃት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቧን ሰላም ለመጠበቅ ዝግጁ የሆነ የማይበገር ወታደራዊ ክንድ መኖሩን ያረጋገጠ ነው።
የጸጥታ ሥጋቶች ይበልጥ ውስብስብ እየሆኑ በመጡበት በዚህ ዘመን ይህ ኃይል ሁልጊዜም ዝግጁ፣ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን የሚቋቋም እና ድል አድራጊ ሆኖ ይቀጥላል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ