የህዝብ ጋሻና የሉዓላዊነት አምባ – የሀገር መከላከያ ሠራዊት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሀገር ጥንካሬ መሠረቶች አንደኛው ለሀገርና ለህዝብ የቆመ፣ ሉዓላዊነትን ለማስከበር የሚሰራ ጥንካሬና ዘመናዊነትን የተላበሰ ተቋም ባለቤት መሆን ይጠቀሳል፤ ይህም ተቋም የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዚህ ረገድ ትልቅ ኃላፊነትን እየተወጣ የሚገኝ ተቋም ነው።
ኢትዮጵያ የነጻነትና የክብር ረጅም ታሪክ አላት፤ በታሪኳ ውስጥ ትልቅ ስፍራን የሚይዙ የሀገር ዳር ድንበርና ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የተደረጉ በርካታ ምዕራፎች አሉ።
የዛሬ መከላከያ ሠራዊት ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት በዘመናዊ የሙያ ብቃት፣ በስልጠናና ተቋማዊ ስርዓት አዳብሮ እየተወጣ ይገኛል።
የመከላከያ ሠራዊት ከዩኒፎርሙ ጀርባ የግል ምቾትን የገታ ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ዋጋን የከፈለ የሀገር ደጀን ነው።
ለአሸባሪዎችና ለሚላላኳቸው ብቻ ሳይሆን ቀጣናውንም ጨምሮ ሊፈጠር ለሚችል የውስጥም ሆነ የውጪ ጠላት ደጀን የሚሆን ነው።
መከላከያ ሰላምን ማጽናትና የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የደምና የአጥንት መስዋዕትነትን ለመክፈል የማይቋረጥ ተነሳሽነትና በጊዜያት የማይናወጥ የሀገር ፍቅርን የተላበሰ ነው።
በሰላሙ ጊዜም የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፣ የሙያ ስልጠናዎች፣ ተቋማዊ ዝመናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡
የመከላከያ አቅም በጦርነት ጊዜ ብቻ የሚለካ አይደለም፤ ሰላም እንዲከበር፣ የሀገር ደህንነት እንዲጠበቅና ህዝብ በደህንነት እንዲኖር በማገዝም ጭምር እንጂ፡፡
ሠራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር እርስ በእርስ በመከባበር፣ ህግን በማስከበር እንዲሁም በሰብዓዊ መተጋገዝ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት አለው፡፡ በመሆኑም የተቋሙ ጥንካሬ በኃይል ብች ሳይሆን በሚያበረክተው ጥቅምም ይለካል፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ዜጎች በአንድ የሀገር ወዳድነት ጥሪ ሲሰለፉና በጋራ ሲያገለግሉ፣ የትብብርና ለጋራ ግብ የመቆም ተሞክሮን ያሳያል፡፡
ይህም ልዩነቶችን በወጥነት በመሸፈን ሳይሆን ልዩነቶችን እያከበሩ በህግና በጋራ ዓላማ የመተባበር መልክ ማሳያ ይሆናል፡፡
የዛሬው ዓለም የደህንነት ተግዳሮት ከባሕላዊው ወታደራዊ አቅም በላይ የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሎጂስቲክስ እንዲሁም የተለያዩ የሙያ ክህሎቶችን ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም የሠራዊቱ የሰው ኃይል በእውቀት፣ በተግባራዊ ስልጠናና ተጠያቂነት ላይ ይመሰረታል፡፡
ተቋሙ ዋናው ሚናው ሀገር መጠበቅ ቢሆንም የተለያዩ የድጋፍ ተግባራቶችንም ያከናውናል፤ ይህም በደህንነትም በልማትም የሚደረገው ተግባር የሠራዊቱን አስተዋፅኦ ይበልጥ ትርጉም የሚያሰጠው ነው፡፡
119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ይከበራል።
በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሠራዊት የድል ጀብዱ በወታደራዊ አቅምና በጦር ሜዳ ድሎች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፤ ሀገር በሚጠብቅበት፣ ሰላምን በሚያስከብርበት እንዲሁም ባስፈለገው ጊዜ ሁሉ ህዝቡን በሚደግፍበትና ኃላፊነቱን በሚወጣበት ልክ የሚታይ ይሆናል፡፡
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
በቤተልሔም ግርማ