Fana: At a Speed of Life!

የድል ሠራዊት፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የዘመናት ቅብብሎሽ ጋሻ የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሀገር ክብር እና ለህዝቦች ደህንነት ሲዋደቅ እዚህ ደርሷል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ በልጆቿ ብርቱ ክንድ ታፍራ እና ተከብራ ለዘመናት ዳር ድንበሯ ተጠብቆ ዛሬ ላይ ለመቆም በቅታለች፡፡
119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን “የድል ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ይከበራል፡፡
በዓሉ ሲከበር ሠራዊቱ የሀገርን ድንበር ከመጠበቅ ባሻገር፣ የህዝቦችን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በተለያዩ ግንባሮችና የግዳጅ ቀጣናዎች ያስመዘገባቸውን ስኬቶች፣ ያሳየውን የሀገር ፍቅር እና ለኢትዮጵያ ህልውና የከፈለውን የላቀ መስዋዕትነት በማሰብ የሚከበር ነው፡፡
የኢትዮጵያ አባቶች ስለ መከላከያ ሠራዊት ሲመሰክሩ ሠራዊቱ ሳይታጠቅ እንኳን ወኔው በዓለም የታወቀ የማንንም ሀገር ለመውረር ተነስቶ የማያውቅ ለመውረር የመጡትን ደግሞ አሳፍሮ የሚመለስ ሠራዊት መሆኑን ይመሰክራሉ፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንደ ዛሬው ዘመናዊ መሣሪያ ሳይታጠቅ እንኳን በዓለም ስሙ የታወቀ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በማረጋገጥና የሀገርን ሉዓላዊነት በመጠበቅ የበረታ ሠራዊት ነው፡፡
ይህ ሠራዊት ለህዝብ ደጀን ሆኖ ዳር ድንበርን ከማስጠበቅ ባላፈ የህዝብ ልጅ ሆኖ በማህበረሰቡ የሚከሰቱ የሰራው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲኖሩ ፈጥኖ ደራሽ እና እምባ አባሽ ነው፡፡
በዓለም አቀፍ የሰላም ተልዕኮዎችም ቢሆን የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ በከፍተኛ ዲሲፕሊን ከፍ አድርጎ የሚያውለበልብ ምልክት ነው፡፡
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.