Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አባልነት ብቸኛዋ የአፍሪካ ዕጩ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት አባልነት አፍሪካን በመወከል ብቸኛ ዕጩ ሆናለች አለ የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡
ሚኒቴሩ እንዳለው÷ እጩነቱ ሀገሪቱ ለዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ የምታደርገውን ዘላቂ አስተዋፅኦ እና የአፍሪካን ጥቅም በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን መድረክ ለማስከበር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን መስራች አባል እንደመሆኗ ባለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ያካበተችውን ተቋማዊ ልምድ፣ የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም በአቪዬሽን ደህንነት፣ ጥበቃና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ያላትን ጠንካራ ስም ይዛ ለምክር ቤት አባልነቱ መቅረቧን አመልክቷል።
አፍሪካን ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእሲያ ጋር የሚያገናኝ ስልታዊ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ያላት ኢትዮጵያ በሰፊ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቷ፣ በዘመናዊ የአቪዬሽን ሥልጠና፣ በጥገና እንዲሁም በካርጎ አገልግሎት አቅሟ የዓለም አቀፍ ትስስርን ማጠናከሯን ቀጥላለች ተብሏል።
ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል ሆና ስትመረጥ የድርጅቱን ዓላማዎች ለማሳካት፣ ይበልጥ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ አቪዬሽንን ለማስፋፋት፣ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር ሀገራት ከዘላቂ የአቪዬሽን ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለመሥራት ቃል መግባቷን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.