Fana: At a Speed of Life!

ሕገ-ወጡ ሕወሃት በመቐለ የፈጸመው ውድመትና ዝርፊያ ለትግራይ ህዝብ የማያስብ መሆኑን ያሳያል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕገ-ወጡ ሕወሃት በመቐለ ከተማ የፈጸመው ውድመትና ዝርፊያ ለትግራይ ህዝብ የማያስብ መሆኑን ያሳያል ተባለ፡፡
ሕገ-ወጥ ቡድኑ ከመቐለ ከተማ ለቆ በወጣበት ወቅት በክልሉ ዋና ዋና አስተዳደራዊና የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት አድርሷል ፤ ይህ ድርጊቱም ቡድኑ ለትግራይ ምድርና ሕዝብ አሳቢ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።
በከተማዋ በሚገኙ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስተዳደራዊ ሕንፃዎች፣ በትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና በምክር ቤቱ እንዲሁም በሌሎች የመንግሥት ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመትና ዝርፊያ፣ የሕዝብን ንብረትና የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን ያላገናዘበ አካሄድ መከተሉን ያመላክታል።
በተደረሰው ሰፊ ጉዳት ምክንያት የከተማዋ የአስተዳደር ሥራዎችና የሕዝብ አገልግሎቶች መስተጓጎላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም መቐለን እንደገና ለማቋቋም ተጨማሪ ሀብት፣ ጊዜና ጥረት እንዲጠይቅ አድርጎታል። በተጨማሪም የክልሉን ተቋማዊ አቅም በእጅጉ አዳክሞታል።
በአሁኑ ወቅት መንግሥት የተጎዱትን ተቋማት መልሶ በማቋቋምና የሕዝብ አገልግሎቶችን በተመለሰ መልኩ ለማስቀጠል የሚያስችሉ የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በግዛቸው ግርማዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.