Fana: At a Speed of Life!

እየተጠናከረ የመጣው የኢትዮ-ሩሲያ ግንኙነት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከ130 ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል።
በዓድዋ ጦርነት ወቅት የሩሲያ ህክምና ቡድን በጦርነቱ ላይ በመገኘት የቆሰሉ ተዋጊዎችን የህክምን አገልግሎት በመስጠት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በዘመናት መካከል እያደገ እና እየጎመራ መጥቶ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሁለቱ ሀገራት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፋሺስት እና የናዚ ስርዓቶች የተዋጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ለሶቪዬት ህብረት ቀዩ ጦር እርዳታ መስጠቷም በታሪክ ተመዝግቧል፡፡
ንጉሰ ነገስቱ በፈረንጆቹ 1945 የተገነባውን የሩሲያ ባህል ማዕከል መርቀው ከፈቱ፡፡ በፈረንጆቹ 1959 እና 1967 ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሩሲያን ጎብኝተዋል፡፡ ሶቪየት ህብረት ለኢትዮጵያ አሰብ ወደብ ላይ የነዳጅ ማጣሪያን ገንብታለች፡፡
በደርግ ዘመንም ሀገራቱ በሚከተሉት ተመሳሳይ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ምክንያት በጥብቅ ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ሁሉን አቀፍ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና አይዲዮሎጂያዊ አጋርነት ነበራቸው፡፡
ኢትዮጵያዊያን በተለያየ ዘርፎች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር ሞስኮ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፡፡
በኢህአዴግ ወቅትም ሩሲያ የእዳ ስረዛን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነትና ወዳጅነት አስቀጥላለች።
ይህ አጋርነት እና ወዳጅነት በመደመር መንግሥትም ተጠናክሮ ቀጥሎ የኢትዮጵያና የሩሲያ ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በሁለትዮሽ እና በባለ ብዙ ወገን መድረኮች ሁሉ ከፍተኛ ትብብር እና መናበብ ያለበት ነው፡፡ ይህም በተባበሩት መንግሥታት፣ በብሪክስ፣ በሩሲያ-አፍሪካ እና በሌሎች መድረኮች የታየ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ሶስት ጊዜ ሞስኮን ጎብኝተዋል፡፡
በ3ኛው የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት ላይ እየተሳተፉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለቱ
ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን በተመለከተ ነው ውይይት ያካሄዱት።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው በሩሲያና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ወዳጃዊ ግንኙነት ሁል ጊዜም ፍሬያማና ገንቢ በመሆኑ ለግንኙነቶቻችንን ከፍተኛ ዋጋ እሰጣለሁ ብለዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ፕሬዚዳንቱ አንስተው፤ ከጥር እስከ መስከረም ባሉት ወራት ብቻ የ2025 ዓመታዊ ድምርን በእጥፍ በልጦ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት በኃይል፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በህዋ ምርምር ሳይንስ፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፎችም ያላቸው ትብብር እየተጠናከረ እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.