ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
በውይይታቸውም በአህጉራዊ አስተዳደር፣ አካታች የፖለቲካ ሂደቶች፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ የልማት ጉዳዮች እንዲሁም የአፍሪካን አመራር በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።