ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ክህሎት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በቁርጠኝነት እየሰራች ነው – አቶ በረከት ፍስሃጽዮን
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ክህሎት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በቁርጠኝነት እየሰራች ነው አሉ የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሃጽዮን፡፡
ሚኒስትሩ ከኮፕ 31 ጎን ለጎን በተካሄደ “ዝቅተኛ የካርበን ኢኮኖሚን ለመገንባት ክህሎትን ማሳደግ እና የስራ እድል ፈጠራን ማፋየን” በተሰኘው የውይይት መርሐ ግብር ተሳትፈዋል፡፡
አቶ በረከት ፍስሃጽዮን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በሰው ሀብት ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማስፋፋት እና ፍትሐዊ የሆነ አረንጓዴ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራች ትገኛለች።
አዲስ አበባን ለኮፕ-32 ጉባኤ ዝግጁ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት፣ የታዳሽ ኃይል ማፋጠን እና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለወጣቶች በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደፈጠሩ እና አሁንም አዳዲስ አጋጣሚዎችን እየከፈቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ክህሎት ልማት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በእመቤት ሲሳይ