Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለኮፕ – 32 ጠንካራ ዝግጅት እያደረገች ነው – ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለኮፕ – 32 ጠንካራ ዝግጅት እያደረገች ነው አሉ የገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፡፡
ኢትዮጵያ በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ባለው የኮፕ – 31 መድረክ የራሷን ፓቪሊዮን ከፍታ እያስተዋወቀች ትገኛለች፡፡
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቱርኪዬ አንታሊያ የተከፈተው የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን የኢትዮጵያን የኮፐ – 32 ዝግጅት ለማሳየት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
በቱርኪዬ አንታሊያ የተከፈተው የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን ዓለምን ለማደራደር አቅም ያላት ዝግጁ የሆነች እና ጉዳዩን የተረዳች ሀገር መሆኗን ማሳያ መድረክ ነው ብለዋል፡፡
መድረኩ ኢትዮጵያን የምናስተዋውቅበት እና ለኮፕ – 32 አዘጋጅነት ዝግጁ መሆናችንን የምናሳይበት ነው ያሉት ሚኒስትሯ በዚህ ፓቪሊዮን 60 የሚሆኑ መሰናዶዎችን ለማዘጋጀት መታቀዱን አመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም ወዳጅነት የምናፈራበት፣ ኢንቨስትመንቶችን የምንስብበት ለስራው የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የምንነጋገርበት እና አጋርነት የምንፈጥርበት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ እና የሚመጥን እንዲሁም ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተቻቸውን የስልጣኔ፣ የምርት እና የማዕድን ሀብቶች የምናሳይበት ነው ብለዋል፡፡
ከኮፕ – 32 ዝግጅት ባለፈ ሰዎች ኢትዮጵያን ማየት አለብን እንዲሉ እና ወደ ኢትዮጵያ ማቅናትን እንዲያስቡ ለማድረግ ሰፊ ስራ እንሰራለን ነው ያሉት ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት አየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 31) ‘ከቃላት ባለፈ ወደ ተግባርና አፈጻጸም መሸጋገር’ በሚል መሪ ሀሳብ በቱርኪዬ አንታሊያ ከተማ በዛሬው ዕለት መካሄድ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.