በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 33 ሚሊየንን ተሻገረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 33 ሚሊየንን መሻገሩ ተሰምቷል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ33 ሚሊዮን በላይ ሆኗል፡፡
እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ998 ሺህ በላይ መሆኑን መረጃው ያመላክታል ፡፡
ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችም ከ24 ሚሊየን 411 ሺህ በላይ ደርሰዋል፡፡
አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ኮሎምቢያ ቫይረሱ ከጸናባቸው የአለም አገራት ቀዳሚ በመሆን ከአንድ እስከ አምስት ተቀምጠዋል፡፡
ፔሩ፣ ስፔን፣ ሜክሲኮ፣ አርጀንቲናን በመከተል ደቡብ አፍሪካ በአስረኛ ደረጃ የተቀመጠች ሲሆን ኢትዮጵያ ከ215 የዓለም አገራት መካከል በ49ኛ ደረጃ ተጠቅሳለች፡፡
ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር