በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 73 ሺህ አለፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 73 ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 631 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 632 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 73 ሺህ 332 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመላክታል።
ከዚያም ባለፈ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ÷በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 170 መድረሱንም ተመላክቷል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ 330 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 30 ሺህ 363ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
41 ሺህ 797 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 249 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።
በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 256 ሺህ 182 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።