የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ቦታ ጽዳት ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጪው ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በርካታ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በማከናወን ላይ ነው።
በዚህም የቦታውን ማረጋገጫ ካርታ ለአባ ገዳዎች መስጠት፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ወጣቶች የስምሪት አቅጣጫ መስጠት፣ ከአባ ገዳዎች ጋር በመሆን ስለ ኢሬቻ በዓል ምንነትና እሴት ግንዛቤ መስጠት ይገኝበታል ተብሏል ።
ከዚያም ባለፈ ከተለያየ አካባቢ የሚመጡት ታዳሚዎች የሚስተናገዱባቸው ፕሮግራሞችን ማውጣት እንዲሁም በዓሉ የሚከበርበት ቦታ የመጎብኘትና ጽዱ የማድረግ ስራዎችን በመሰራት ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።