Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡

የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ዶክተር ማተቤ ታፈረ እንደገለፁት አካዳሚው የሰው ሀይል፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የማስተማሪያ ክፍሎች፣ የማሠልጠኛ እና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊና ምቹ ህንፃዎችን አሟልቷል፡፡

አካዳሚው በክልሉ ብቃት ያላቸው መሪዎችንና ሙያተኞችን በማፍራት ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና የህዝቡን የመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት መዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡

የክልሉን አመራርና ባለሙያዎችን አቅም በመደበኛ ትምህርት በማሳደግ፣ የአመራር፣ የልህቀትና የምርምር ማዕከል ለማድረግ፣ የክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ለማከናወንና የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቷልም ነው ያሉት፡፡

በተያዘው አመት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ ለክልሉ ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.