መቐለ ዩኒቨርስቲ ለ8 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መቐለ ዩኒቨርስቲ ለ8 ምሁራን ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።
የዩኒቨርስቲው ቦርድ በዛሬው ዕለት ለ8ቱ ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረጉን አፅድቋል።
በዚህም መሰረት ዶክተር አፈወርቅ ሙሉጌታ ፣ ዶክተር ኢብራሂም ፍትዊ ፣ ዶክተር ክንፈ አብርሃ ፣ ዶክተር ምሩፅ ሃጎስ ፣ ዶክተር ገብረህይወት ታደሰ ፣ ዶክተር መሀመድ ኢስማኤል ፣ ዶክተር አለማየሁ ባይራይ እና ዶክተር ሀፍቱ በርሄ ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።