Fana: At a Speed of Life!

የመስከረም ወር ዓለም ላይ ሞቃታማው ወር መሆኑን ተመራማሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስከረም ወር ዓለም ላይ ሞቃታማው ወር መሆኑን ተመራማሪዎች ገለጹ፡፡

የዘንድሮው መስከረም ወር ካለፈው አመት መስከረም ወር ጋር ሲነጻጸርም የሙቀት መጠኑ በ0 ነጥብ 05 ዲግሪ ሴሊሺየስ ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የምድር ምልከታ ፕሮግራምም በሳይቤሪያ አርክቲክ ውስጥ ያለው ሙቀት ከአማካይ በላይ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጿል።

የሙቀት መጨመሩ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው የበካይ ጋዝ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመሩ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

ከሙቀት መጠኑ መጨመር ባለፈም ሰደድ እሳትና ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ለከባቢ አየር መበከል አይነተኛ ማሳያ መሆናቸውን ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡

እንደተመራማሪዎቹ ገለጻ ሃገራት የአየር ንብረት ፖሊሲዎቻቸውን ሊያጤኑት ይገባል፡፡

ምንጭ፥ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.