Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ያካሄዱትን ድርጅታዊ ኮንፈረንስ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ለሁለት ቀናት አዲስ አበባን በብልጽግና ጎዳና ማራመድ የሚችል አመራር እንገነባለን በሚል መሪ ቃል ሲያካሂዱት የነበረው ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ተጠናቋል፡፡

የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡

የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ድርጅታዊ ኮንፈረንስ የአቋም መግለጫ

የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ለሁለት ተከታተይ ቀናት “አዲስ አበባን በብልጽግና ጎዳና ማራመድ የሚችል አመራር እንገነባለን ” በሚል መሪ ቃል ስናካሂድ የነበረው ድርጅታዊ ኮንፈራንስ መድረክ ሲጠቃላል ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ በመጠንበት የለውጥ ጉዞ ሂዳት ውስጥ በሀገራችን እንደ አጠቃላይና በከተማችን በተለየ ሁኔታ ያስመዘግበናቸውን ውጤቶች፣ በሂዳቱ ያገጠሙንን ተግዳሮቶችንና በቀጣይ የርብርብ አቅጣጨዎች በማንሰት በዝርዝር ተወያይተናል፡፡

በእነዚህ የለውጥ ዓመታት መዋቅራችንና ምልአተ ህዝቡን በተደራጀ መንገድ ወደ ተግባር እንቅስቃሴ በማስገባት በአንድ በኩል ከተማችንን የሚያዘምኑ በሌላ በኩል የነዋሪዎችን የኑሮና የህይወት ጉስቁልና የሚያሻሸሉ ድሀ ተኮር ፕሮግራሞችን ቀርፀር በስኬት መፈፀማችንን አይተናል፡፡

እነዚህ ስኬቶች እንዳሉ ሆነው የለውጡ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግብ ተደርጎ የሚወሰደው ሁለንተናዊ ብልጽግና በማረጋገጥ የህዝቡ ኑሮ ሁኔታን ማሻሻል፣ ዴሞክራሲን ማስፈን፣ መልካም መንግሥታዊ አገልግሎት አቅርቦትን እያረጋገጥን መሄድንና ለነዋሪዎች የምትመችና ተመራጭ አዲስ አበባን መፍጠር ነው፡፡ከዚህ አንፃር በቁጭትና በጊዜ የለንም መንፈስ የከተማችን ቁልፍ ፈተና የሆኑትን የስራ እድል ፈጠራ፣የትራንስፖርት ችግር፣የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት፣የውሀ፣የመብራት፣የመኖሪያ ቤት እጥረት እና ሌሎች የአገልግሎት አቅርቦቶችን ለማሻሳልና ኅዝብን ለመካስ ያለ ትንፋሽ መስራት እንዳለብን ተግባብተናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጀማመርናቸው የለዉጥ ሥራዎች ከህብረተሰቡ የመለወጥ ፍላጐት አንፃር ሲታይ አሁንም ሠፊ ሥራ የሚጠይቁን አንገብጋቢ የልማት ጥያቄዎች፣ መልካም የሆነ መንግሥታዊ የአገልግሎት አቅርቦት ጥያቄዎች እንዲሁም ለዉጡን ለመቀልበስ የሚታትሩ የአፍራሽ ኃሎች እንቅስቃሴ ተደማምሮ የተጋረጡብን ፈተናዎች በብቃት ለማለፍ የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያችንን በማጎልበትና ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ለላቀ ውጤት ቀን ከሌሊት መስራትን እዲሁም ለህዝብ ጥቅም ሲባል ሁሉንም ዓይነት መስዋዕትነት መክፈልን እንደሚጠይቅ በኮንፈራንሱ በዝርዝር ተገምግሟል፡፡

ከዚህም በመነሳት እኛ የዚህ ኮንፈራንስ መድረክ ተሳታፊ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ ሁኔታዎችን በለውጥ መንፈስ ስህተቶቻችንን በፊጥነት አርመን ኃላፊነት በተሞላበት አግባብ ህዝባችንን ለመካስና በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ ውጤት ለማስመዝገብ በጥልቀት የመከርን ሲሆን የሚከተሉትን ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

1. ፓርቲያችን ብልጽግና አሁን ላለንበት መድረክ ሊመጥን የሚችል የአመራር ስምሪት ማረጋገጥ፣ የአመራር ክፍተት መሙላት፣ ግድፈቱን ማረም፣ በየደረጃው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር የሚያስችል የግንባታ ስራ መስራትና የማበረታት አቅጣጫ ተከትለን መስራት እንዳለብን በኮንፈረንሱ በዝርዝር ገምግመን ተግባብተናል፡፡ ለዚህ ተግባር ስኬት ዋነው መሰረት ደግሞ የብልጽግና መዋቅራችን በአደረጃጀትና በአሰራር እንዲጠናከር በማድረግ በተለይ ከአመራር ምደበ ጋር ተያይዞ በየደረጃ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ የፓርቲ ስራችን እግር እንዲተክልና ተቋማዊ አቅሙ እንዲጠናከር ለማድረግ ከምን ጊዜውም በላይ ልዩ ፖለቲካዊ ትርጉም በመስጠት የመሪነት ሚናችንን ለመወጣት ቆርጠን የተነሰን መሆናችንን እናራጋግጠለን፡፡

2. ያሳለፍናቸው ሁለት የለውጥ አመታት ሀገራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታው በእጅጉ የተወሣሠበና በአገር ደረጃ የተጀመረው ለውጥ ሥር የሰደደና ገና የሰከነ ፖለቲካዊ መድረክ ባለመፈጠሩ ምክንያት ፓርቲያችን ከውስጥም ከውጭም ቀላል የማይባል ተግዳሮት ሲገጥመው ቆይቷል፡፡ሂደቱን የሚመራው አመራር ውስጣዊ ጥራቱን ጠብቆ፤ ከጎራ መደበላለቅ ጸድቶ፤ ሌብነትን እየደፈቀ በመደመር ጎዳና ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ ውጤታማ በሆነ አጨራረስ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር በጽናት መታገል እንደሚያስፈልግ ኮንፈራንሱ አጽንዖት ሰጥቶ ተወያይቷል፡፡ ስለሆነም አመራራችንና መዋቅራችን በለውጥ ሀይሉና በፅንፈኛው መሀከል ያለውን ልዩነት ተገንዝቦ ከመታገል ይልቅ በሌብነትና ብልሹ አሰራር ያልተገባ ትስስር በመፍጠር ከህገ ወጥ ደላሎች፣እላፊ ጥቅም ከሚፈልጉ ባለሀብቶች፣የፓርቲ ውግንና ከሌላቸው አመራሮች፣ለህጉ ተገዥ ካልሆኑ የፍትህ አካላት እና በየደረጃ ካለ ማገልገልን ክብር አድርጎ ከማይቆጥር ባለሙያ ጋር በመሆን የጠፉ ጥፋቶችን ሁሉ በትግል እና በተጠያቂነት በማረም፤ ለዚህ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ አሰራርና መመሪያዎችን እንዲሁም መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን በማከናወን መፍትሄ መስጠት፤ ቀድሞ ሲታገል ያልነበረ አንዳንዶች ደግሞ በችግሩ ውስጥ ያሉ አካላት ጭምር ችግሩ እያወሳሰቡና ህዝብ ውስጥ ጥርጣሬ በመፍጠር ህዝቡ አመራሩ ውስጥ ያለውን እምነት እንዲሸረሸር የሚያደርጉ ጉዳየዮች በማረም በአኛ ድክመት ምክንያት ለውጡ ምህዋሩን ስቶ ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ እንዳይደናቀፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ ሌት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳንል ለመስራት ቃል እንገበላን፡፡

3. ከመንግስት አገልግሎት አንጻር በተለይም የመሬት አስተዳደር(የመሬት ወረራ፣የሪል እስቴት ፍቃድ አሰጣጥ)፣ የበጀትና የኮንትራት አስተዳደር፣ ከገቢዎችና ንግድ ሥርዓታችን(የግብር አሰባሰብ፣የፍጆታ እቀዎች አየር ባየር ንግድ)፣ የፍቃድና የቁጥጥር ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ ብልሽቶች ብልጽግና ፓርቲን በህዝብ ዘንድ አመኔታ የሚያሳጡ ከመሆናቸዉም በላይ የለዉጥ እና የብልጽግና ጉዞ የሚጎዱ፣ የአመራር ስርዓታችንን የሚፈታተኑ እና የመዋቅራችን አቅም የሚያዳክሙ አደገኛ የዉስጠ ፓርቲ ተግዳሮት እንደሆኑ ገምግመናል፡፡ በተለይም የመሬት አስተዳደር ስርአታችን ዉስጥ በአንድ በኩል መታረም የሚገባቸዉ ችግሮችን በፖለቲካዊ ፣አስተዳደራዊ እና ህጋዊ መሳሪያዎቻችን በተቀናጀ አግባብ በመጠቀም ፊት ለፊት መጋፈጥ የሚጠይቅ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለግምታዊ ወሬዎች የሚዳርጉ ሁኔታዎችን እያጣራን እዉነትነት ላላቸዉ ጉዳዮች በመንገዳችን ላይ ሆነን እየተጋፈጥን የምንቀጥል መሆኑ ሊሰመርበት እንደሚገባ በጥልቀት አይተናል፡፡

በመሆኑም በየደረጃው የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችና፣ የጥቅም ትስስር (ኔትወርክ) እና ሌብነትን ጠንካራ የፓርቲና የመንግስት ተቋም በመገንባት፣ በጠንካራና በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ ሁሉንም ህብረተሰብ ከመንግስት ጎን ማሰለፍ የሚችል ስርዓት በመዘርጋት ውዝፍ ስራዎቻችንን አጠናቀን ፍትሀዊና ተደራሽ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እናሰፍናለን፡፡

4. የወጣቶችና ሴቶችን ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ እያጋጠሙ ያሉ የአስተሳሰብና የተግባር ማነቆዎችን በመፍታት በከተማው የወጣቶችና ሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማጠናከር ተገቢ ነው፡፡ በተለይ በተቀጣጠለው ለውጥ በወጣቱ ዘንድ የተቀሰቀሰው የልማት ተስፋ በመልካም አስተዳደር እጦት ሊደናቀፍ አይገባውም፡፡ ስለሆነም የከተማችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማራጋገጥ በአንድ በኩል በኛ ዘንድ የሚታዩ የተንዛዙና ፍትሃዊ ያልሆኑ፤ ከብልሹ አሰራርና ሌብነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በሌላ በኩል ደግሞ የወጣቱን የአስተሳሰብ ችግር በመግራት፤ የዘላቂነትና የአዋጭነት ችግር የሚስተዋልባቸው ዘርፎችን ለይቶ በማስተካከል ወጣቱን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ማድረግ የአመራራችን አንገብጋቢ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገበ በኮንፈራንሱ ተስማምተናል፡፡ ስለሆነም በስራ እድል ፈጠራ ስራችን በግሉ ዘርፍ ጭምር የወጣቱ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከመስራት ጎን ለጎን ስብዕና ግንባታ ላይ አተኩረን አገር ወዳድ እና የስራ ባህሉ የተቀየረ ዜጋ እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥተን ለመተግባር ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጠለን፡፡

5. አዲስ አበባችን ህብረ ብሔራዊ ናት፡፡ የብዙ ማንነቶችና የብዙ ቋንቋና ባህል መገኛ ከተማ ናት፡፡ ከዚህ አንጻር የሃገራችንና የከተማችን ህዝቦች እርስ በእርስ ተከባብረውና ተፈቃቅደው እንዲኖሩ የሚያደርግ የእለት ተእለት የፖለቲካ ስራ መስራት ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻር ለሰላም መደፍረስ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ በዝርዝር በመፈተሸና በጥልቀት በማየት ችግሮቹ በዘላቂነት የሚፈቱበትን አግባብ መከተል እንደሚያስፈልግ በዝርዝር ገምግመናል፡፡ መላዉ የመዋቅራችን አካላት ህዝቡን በማሳተፍ የከተማችን ሰላምን እንዲያረጋግጥ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር እንዲሁም ህዝቡ ለልማት የሚያደርገዉን ተሳትፎ በማጠናከር፤ የፀጥታና የፍትህ አካላት ህዝቡን በማሳተፍ አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም የሚፈጥር ስራ እንዲሰሩ በቅርብ በመከታተልና በመደገፍ በከተማችን ከምን ጊዜውም በላይ አስተማመኝ ሰለም ለማራጋገጥ የመሪነት ሚናችንን በትጋት በመወጠት ላይ የነበሩብንን ጉድለቶች ለማረም ዝግጁነታችንን እያረጋገጥን በህዝባችን ውስጥ ትርምስ ለመፍጠር የተዘጋጁ አፍራሽ ሀይሎችን እንደ ወትሮው ሁሉ ከፀጥታ መዋቅሩ እና ከሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ ጋር ተቀናጅን ከተማችንን ወደ አሰብነው የከፍታ ማማ እናደርሳለን፡፡

6. የአለማቀፍ ተቋማት መቀመጫ፣የአፍሪካ መዲናና ህብረ ብሄራዊቷ ከተማችን አዲስ አበባ ገፅታዋን አጉልቶና አጎልብቶ የሚያሳይ ህዝብና መንግስትን የሚያቀራርብ፣ትውልድን የሚያቀና ሚዛናዊና ዘመናዊ የሆነ፣ስናጠፋ የሚሞግተን የተለያዩ የተግባቦት መንገዶችን በመጠቀም ለህዝብ ድምፅ በመሆን ከሚያገለግሉት ሚዲያዎች ጋር ተቀራርበን እንሰራለን፡፡

7. በ2013 ዓ.ም የ መሚደረገዉ ሀገራዊ ምርጫ እንደ ከተማችን ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው ምርጫ በማካሄድ ፓርቲያችን በከተማው ምክር ቤቶች አብላጫ ድምጽ በማግኘት አሸንፎ እንዲወጠ ከምንጊዜውም በላይ ተግተን ለመስራት ቃል እንገበለን፡፡

አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን !!
ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.