Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የቤተርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተክርስቲያን በልማት፣ በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ መስራት ይጠበቅባታል ብለዋል።
የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን አረጋውያንን በመጦር እና ህጻናትን በመንከባከብ የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን እንዲሰጡም ፓትሪያርኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቆይታው የሁሉንም አህጉረ ስብከት አመታዊ የስራ አፈጻጸም በማድመጥ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በጉባኤው ላይ የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስን ጨምሮ ብጹአን ሊቃነ ዻዻሳት፤ የመምሪያ ሃላፊዎች የምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡
በሲሳይ ጌትነት
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.