Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መልኩ ወደ አሜሪካ ሊገቡ የነበሩ ጥንታዊ የካሜሩን የድንጋይ ላይ ቅርጻ ቅርጾች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የጉምሩክ ባለሥልጣናት ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም በሕገወጥ መንገድ ከካሜሩን ወደ አሜሪካ ሊገባ የነበረ በርካታ ጥንታዊ የድንጋይ ቅርጻ ቅርጾች መያዛቸውን አስታወቁ።
የድንጋይ ቅርጻ ቅርጾቹ የተያዙት በሚያሚ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ቅርጻ ቅርጾች ኢኮም ሞኖሊትስ በመባል የሚታወቁትና ካሜሩን ከናይጀሪያ ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ የተገኙ ናቸው ተብሏል።
ከ200 እስከ 1000 ዓመተ ዓለም የተሰሩ ሳይሆኑ እንደማይቀሩም ባለሙያዎች ገልጸዋል።
እያንዳንዳቸው በልዩ ሁኔታ በሰው የፊት ገጽታ በጂኦሜትሪ ንድፎችና በጥንታዊ ጽሑፎች የተጌጡ ናቸው ተብሏል።
የስነ ፅሁፍና ቋንቋ ምሁራንም ቅርጾቹ ላይ የታዩት ምስሎች የሰውን ልጅ ጥንታዊ የስነ ፅሁፍና መግባቢያ መንገዶችን የሚያመላክቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአሜሪካ የድንበር ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት የድንጋይ ቅርጻ ቅርጾቹ ወደ ካሜሩን እንደሚመለሱም አስረድተዋል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.