የልዩ ዘመቻዎች ሀይል የኮማንዶ ትርኢት ተካሔደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ33ኛ ዙር መሰረታዊ ኮማንዶና የ10ኛ ዙር ልዩ ኃይል የፀረ ሽብር ሰልጣኞች የአየር ወለድ ትርኢት በሃዋሳ ከተማ አቀረቡ፡፡
በሄሊኮፍተር በታገዘው ትርኢት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ዘርፍ መመሪያ ኃላፊ ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ተከታትለዋል።
ትርዒቱ የፀረ ሽብር ዘመቻዎችን በብቃት መወጣት እንደሚቻል የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ተመሳሳይ ትርኢቶች በቶጋ ካምፕ እና በወንዶ ጢቃ ካምፕም ተካሂዷል።
በሀይለየሱስ መኮንን