Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው የሶስትዮሽ ውይይት ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድብ ላይ የሚያደርጉት የሶስትዮሽ ውይይት ዛሬ ይካሄዳል፡፡
 
በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚደረገው ውይይት ሃገራቱ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት አካል ነው፡፡
 
ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ላይ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ከዚህ ቀደም ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
 
የህዳሴው ግድብ ግንባታም የተፋሰሱ ሃገራት የውሃ ተጠቃሚነትና ድርሻ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማያሳርፍ መልኩ እንደሚካሄድም መግለጿ ይታወሳል፡፡
 
በዛሬው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ በሚካሄደው የሶስትዮሽ ውይይት ላይ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ግንኙነት ሚኒስቴር እንደሚሳተፍም ተገልጿል።
 
ባሳለፍነው ወር መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድርድሩ ይቀጥላል ተብሎ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት ስድስት ሳምንታት ተቋርጦ ቆይቷል።
 
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከሶስቱ ሃገራት መሪዎች ጋር ተወያይተው ድርድሩ እንደገና እንዲቀጥል በተስማሙት መሰረት ነው የሶስትየሽ ድርድሩ ካቆመበት የሚቀጥለው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.