Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ከነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነበር፡፡

በወቅቱ ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች በውሃ ተውጠው እንደነበር ይታወሳል።

ነገር ግን አሁን አንድ ዩኒት ወደስራ ማስገባት በመቻሉ ጣቢያው በከፊል ስራ የጀመረ ሲሆን ቀሪውን አንድ ዩኒት ስራ ለማስጀመር በሂደት ላይ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.