የአሜሪካ ኮንግረስ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ 900 ቢሊየን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ አፀደቀ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ኮንግረስ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ 900 ቢሊየን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ አፀደቀ፡፡
ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ገንዘብ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ በየግዛት አስተዳዳሪዎች ይሁንታን አግኝቷል፡፡
እርዳታው በቫይረሱ ሳቢያ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ቀጥታ ክፍያን እና የተጎዱ የንግድ እንቅስቃሴዎችን እና ስራ አጦችን መደገፍን የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡
ረቂቁ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን፥ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህግ ሆኖ ይቆይ ዘንድ በፊርማቸው ያረጋግጣሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡
በአሜሪካ ኮሮና ቫይረስ ከገባ ወዲህ እንደ መታደጊያ ማዕቀፍ የተዘጋጁ የማገገሚያ ፕሮግራሞች በዚህ ወር መጨረሻ ይጠናቀቃሉ፡፡
ይህ ደግሞ ከስራ አጥነት ጋር በተያያዘ ድጋፍ የሚያገኙ ወደ 12 ሚሊየን የሚጠጉ አሜሪካውያንን ለችግር የሚዳርግ ይሆናል፡፡
የፀደቀው የእርዳታ ገንዘብ ረቂቅ በርካቶችን ይደጉማል ቢባልም የፀደቀበት ሂደት ግን ከህግ አውጭዎች በኩል ትችት እያስተናገደ ነው፡፡
በርካቶች ረቂቁን በአግባቡ ሳያዩትና ሳያነቡት ይፀድቅ ዘንድ ይሁንታ ሰጥተዋል በሚል ወቀሳ ቀርቦበታል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!