Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በኮሮና ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ60 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ60 ሺህ መብለጡን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል አስታወቀ፡፡

ማዕከሉ እስካሁን ቫይረሱ በአጠቃላይ የ60 ሺህ 254 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል ብሏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ በወረርሽኙ በጽኑ የተጎዳች ሀገር ስትሆን በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ የተያዙ እና ለሞት የተዳረጉ ሰዎች ያሉባት በመሆን በቅድሚያ ትጠቀሳለች፡፡

ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ቱኒዚያ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ቫይረሱ የጸናባቸው ሃገራት በመሆን እስከ አምስተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡

እንደ ማዕከሉ መረጃ እስካሁን 2 ሚሊየን 145 ሺህ 138 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እስካሁን ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ79 ሚሊየን 86 ሺህ በላይ ሲሆን ከ1 ሚሊየን 738 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአንጻሩ ከ55 ሚሊየን 674 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲኤ.ን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.