Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የገለልተኛ አማካሪ ቡድን አቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የገለልተኛ አማካሪ ቡድን አቋቋመ፡፡
በአማካሪ ቡድኑ ምስረታ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራ ÷ ክልሉ በአሁኑ ወቅት እዚህም እዚያም የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ የገልተኛ አማካሪ ቡድን ማዋቀሩ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም ይህ ገልተኛ አማካሪ ቡድን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን በሠላም እና በፀጥታ ዙሪያ በማማከር በኩል ትልቅ ሃላፊነት ያለበት ነው ብለዋል።
የገለልተኛ አማካሪ ቡድኑ ምስረታን አስፈላጊነት በተመለከተም የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ስዩም ጋሳ ለተሰብሳቢዎቹ ገለፃ አድርገዋል።
በምስረታ ፕሮግራሙ ላይ ከተለያዩ የማህበረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራ የአማካሪ ቡድኑ ዋና ሰብሳቢ ሆነው ሲመረጡ አቶ ዝናው ሰርሚሶ ደግሞ በምክትል ሰብሳቢነት መመረጣቸውን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.