Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የጤና ኢንሹራንስ አገልግሎት ከጀመረ ረጅም ጊዜ ቢያስቆጥርም በተፈለገው ደረጃ እንዳልተሰራ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የጤና ኢንሹራንስ አገልግሎት ከጀመረ ረጅም ጊዜ ቢያስቆጥርም በተፈለገው ደረጃ እንዳልተሰራ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
በአዳማ ከተማ የጤና ኢንሹራንስ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
በኮንፈረንሱ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ እንዳሉት በጤና ህክምና ወጪ በክልሉ በአንድ አመት ብቻ ከ 2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለከፋ ደህንነት ይጋለጣሉ ብለዋል ።
በክልሉ አገልግሎቱ ከተጀመረ ረጅም ጊዜ ቢያስቆጥርም አገልግሎቱ ግን በተፈለገው ደረጃ መዳረስ አልቻለም ብለዋል።
በዚህም በክልሉ ወረዳዎች 93 በመቶ እንዲሁም በከተሞች 50 በመቶ አገልግሎቱን ማዳረስ ቢቻልም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አባል ማፍራት የተቻለው ግን 43 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል።
የግንዛቤ እጥረት፣የአመራሩ ቆራጥነት ማጣትና፣ የአገልግሎት ጥራት መታጣት ደግሞ ለዚህ በምክንያትነት ተነስቷል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍም የክልሉ መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዶክተር መንግሥቱ በ 2013 በክልሉ አገልግሎቱን መቶ በመቶ እዲሁም ከ70 በመቶ በላይ የክልሉን አባወራዎች የአገልግሎቱ አባል ለማድረግ የጤና ኢንሹራንስ ንቅናቄ መጀመሩን ገልፀዋል ።
በዚህ ወር በ20 ቀን ብቻም ከ 1 ነጥብ 2ሚሊየን በላይ ሰዎችን አባል ማድረግ መቻሉን አንስተው ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል ።
በሀገር ደረጃ የተያዙ አቅዶችን ለማሳካት ጤናማ ዜጋ ወሳኝ መሆኑን ያነሱት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ መንግስት የጤና ሰርአቱ የሀገሪቱን ዜጋ የሚደግፍ ለማድረግ እንዲሁም የጤና አገልግሎቱንም ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በይድነቃቸው ሀይለማርያም
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.