Fana: At a Speed of Life!

ጀጎል ግንብ ዓለም አቀፍ ቅርስነቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚያስችል የ10 አመት የአስተዳደር እቅድ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀጎል ግንብ ዓለም አቀፍ ቅርስ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚያስችል የ10 አመት የአስተዳደር እቅድ መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡
የፌደራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ የ10 አመት የአስተዳደር እቅድ የትግበራ ምዕራፍ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይቱ ላይ የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን እንዳሉት የጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ ተጠብቆ እንዲተላለፍ ከማድረግ አንፃር የአስተዳደር እቅድ ማዘጋጀት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
ቀደም ሲል በነበረው የአስተዳደር እቅድ መሰረት በርካታ ስራዎችን በመስራት ቅርሱ እንዲጠበቅ ማድረግ የተቻለ ቢሆንም በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ ለቀጣይ 10 አመት ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
የጀጎል ቅርስ ከሌሎቹ በተለየ በውስጡ ህዝብ የሚኖርበት ቅርስ ከመሆኑ አንፃር ህዝቡን ያሳተፈ ስራ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
የተዘጋጀው የ10 አመት እቅድ ተግባራዊ እና ውጤታማ እንዲሆን የሚመለከታቸው አካላት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው የምክክር መድረክ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ እና የፌደራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት መገኘታቸውን ከሃረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.