Fana: At a Speed of Life!

በሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል የሚገኙ የአዕምሮ ህሙማንን የሚጎበኝና የሚከታተል የጤና ባለሙያዎች ቡድን ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል በሜቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል የሚገኙ ወደ 800 የሚጠጉ የአዕምሮ ህሙማንን በየቀኑ የሚጎበኝና የሚከታተል የጤና ባለሙያዎች ቡድን መድቦ እየሰራ ነው፡፡

ቡድኑ የአዕምሮ ስፔሻሊስት ሀኪም፣ የስነ ልቦና ባለሙያ፣ የስነ አዕምሮ ነርስ እና የስነ አዕምሮ ማስተርስ ነርሶችን ያካተተ መሆኑን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የባለሙያዎች ቡድኑ በሜቄዶንያ የሚገኙ የአዕምሮ ህሙማን ወደ ጤና ተቋማት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ህክምናውን እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በተቀናጀ መልኩ በሰፊው ስራ መስራት እንዲቻል ሆስፒታሉ ከሜቄዶኒያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማልም ብለዋል፡፡

በስላባት ማናዬ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.