በኔዘርላንድስ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ግብርና ላይ ትኩረት ያደረገ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ዌብናር አካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔዘርላንስ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ግብርና ላይ ትኩረት ያደረገ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ዌብናር አካሄደ፡፡
በኔዘርላንድስ ዘሄግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዲስ አበባ ከሚገኘው የኔዘርላንድስ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ውይይት ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ የደች ኩባንያዎችና የተለያዩ በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
አምባሳደር ሚሊዮን ሳሙኤል በአበባና ሆርቲካለቸር ዘርፍ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የደች ኢንቨስተሮች የሚገኙ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አቅም ያላቸው የደች ኢንቨስተሮች በዚህም ሆነ በሌሎች የግብርና ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የውጭ ኢንቨትመንት ማስፋፋት እና ቴክኖሎጂ ትራንሰፈር ዳይሬክቶሬት ጄነራል አምባሳደር አባቢ ደምሴ ዌቢናሩ በግብርና ዘርፍ ላይ ማተኮሩ ጊዜውን የጠበቀና አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የግል ዘርፉን በግብርና ላይ በስፋት ተሳታፊ ለማድረግ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ከፍተኛ ሪፎርም በማደረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢንቨሰትመንት ኮሚሽንን በመወከል የተሳተፉት የኢንስትመንት ፕሮሞሽን ባላሙያ ወ/ሪት ረድኤት ይሕአለም ባቀረቡት ገለጻ ኢትዮጵያ በግብረና ዘርፍ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሚያደርጓትን ምቹ ዕድሎች እንዳሏት አብራርተዋል፡፡
በተለይም በሰሊጥ፣ በወተትና ወተት ተዋጽኦ፣ የእንስሳት መኖ እና የዶሮ ልማት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት አቅም ያላት መሆኗንና ለዚህ ዘርፍ የተመቻቹ ማበረታቻዎች ላይ ማብራራርያ ሰጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ የኔዘርላንድስ ኤምባሲ የግብርና ካውንስለር የሆኑት ሜወስ ብሮወር ባቀረቡት ገለጻ በአሁኑ ወቅት ከ85 በላይ የሚሆኑ የደች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከዚህም 80 በመቶ የሚሆኑት በግብርና ላይ ተሰማሩ መሆናቸውንና ኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ የወጪ ምርት ተደራሽ ከሆኑ ሀገራት መካከል በዋናነት ተጠቃሽ ሀገር መሆኗን አብራተዋል፡፡
በኔዘርላንድስ ትኩረት የሚሰጥባቸው የግብርና መስኮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውንም ከውጭ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!