Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ቴሌኮም የስራ ሃላፊዎች በገበታ ለሀገር የሚለማውን የወንጪ ፕሮጀክትን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በገበታ ለአገር የሚለማውን የወንጪ ፕሮጀክት እየጎበኙ ነው።

የስራ ሃላፊዎቹ ጉብኝት በዋናነት ቴሌኮሙ በፕሮጀክቱ የሚያከናውነውን ስራ በተመለከተ የመስክ ምልከታ ለማድረግ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች 500 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን በዛሬው ዕለት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ድጋፉ በገበታ ለሀገር ለሚለሙት  የወንጪ ፣ ጎርጎራ እና  ኮይሻ ፕሮጀክቶች እንደሚውል ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።

የተለያዩ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ለገበታ ለሀገር ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.