Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ አቀረቡ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእናት ሆድ ዥንጉርጉርነት የልጆችዋን መልክና ጠባይ አንድ አይነት እንደማያደርገው ሁሉ፤ ከኢትዮጵያ ማህጸን በቅለው፣ የክብር ቦታ አግኝተውና ከሩብ ክፍለ ዘመን ለተሻገረ ጊዜ ሀገር የአስተዳደሩ ሰዎች መልሰው ሀገራችንን ከጀርባ ቢወጓት፥ የእናትን ውርደት በማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ርብርብ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አስታውሰዋል።
 
ዳሩ ግን፥ ዛሬም የጁንታው ሞት ያልተዋጠላቸው ከዥንጉርጉር ማህጸኗ የፈለቁ ሰዎች ከሀገራችን ጠላቶች ጋር እያበሩ፣ የተዛቡ መረጃዎች መርጨቱን የዕለት እንጀራቸው አድርገውታል ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን ኃይሎች እንዳሻቸው መሆን ካልቻሉ ኢትዮጵያ እንድትኖር አይፈልጉም በማለት ነው የገለጹዋቸው።
 
በሕግ ማስከበር ዘመቻው ያጡትን ድል በወሬ ግንባር ለመመለስም ተንኮልን መሣሪያ፣ ሐሰትን ጥይት ማድረግ መቀጠላቸውን ነው የጠቀሱት።
 
በመሆኑም በመላው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፥ ስለ ሀገራችሁና ስለ ወቅታዊው ጉዳይ ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በመናገር፤ የሀገራችንን መልካም ክብርና ስም ለማጥፋት የተነሱ ሰዎችን ድል በመንሳት፤ ሐሰትን በእውነት እንድታሸንፉ ጥሪ አቀርባለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.