ጠ/ሚ ዐቢይና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መከሩ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ጋር በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ስላለው የተጠናከረ ትብብር፣ እንዲሁም በሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስለሚደረግ ድጋፍን በተመለከተ የስልክ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ስለነበራቸው ፍሬያማ ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለፕሬዚዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!