በሁለት ዙር 360 ሺህ ሄክታር መሬት የስንዴ ማሳ በመስኖ እየለማ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው አመት በሁለት ዙር 360 ሺህ ሄክታር መሬት የስንዴ ማሳን በመስኖ የማልማት ስራ መጀመሩን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ሳኒ ረዲ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ከ144 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በስንዴ ዘር ተሸፍኖ በመስኖ እየለማ ይገኛል ብለዋል።
በዚህ አመትም በሁለት ዙር 360 ሺህ ሄክታር መሬትን የስንዴ ማሳን በመስኖ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ሀገሪቱ ከውጭ ከምታስገባው የስንዴ ምርት 50 በመቶውን መሸፈን የሚያስችል እንደሚሆንም ነው ሚኒስትር ዲኤታው የተናገሩት።
የስንዴ ልማቱ ከውጭ ለሚገባ ምርት የሚወጣውን ወጭ ከማስቀረት ባሻገር የሚፈጥረው የስራ እድልም ከፍተኛ እንደሚሆን ታምኖበታል።
ስንዴን በማልማት እስካሁን በተሰሩት ስራዎች ኦሮሚያ ክልል ቀዳሚ ቦታ ሲይዝ በክልሉ 130 ሺህ ሄክታር መሬትን በስንዴ መሸፈን ተችሏል።
በአማራ ክልል ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን አፋር እና ሶማሌ ክልሎችም በተመሳሳይ እያለሙ ይገኛል።
ሌሎች ክልሎችም ወደ ስራው እየገቡ ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው÷ አሲዳማ የሆኑ መሬቶችንም ወደ ስንዴ ልማት ለማስገባት አሲዳማነታቸውን የማከም ንቅናቄ ስራ ይጀመራል ብለዋል።
የሁለተኛው ዙር ስራ ከዚህ ወር በኋላ የሚጀመር ሲሆን በአመቱ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚሰራበት ይሆናልም ነው ያሉት።
በስንዴ ከሚለማው መሬት ውስጥም በሄክታር ከ40 ኩንታል በላይ ምርትን ለማግኘት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
በስንዴ ለሚለማው መሬትም ከ200 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር መሰራጨቱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በዙፋን ካሳሁን
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!