Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የጉዞ እና ቱሪዝም ምክር ቤት የጉዞ ደህንነት ማረጋገጫ ዕቀውቅና አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የጉዞ እና ቱሪዝም ምክር ቤት የጉዞ ደህንነት ማረጋገጫ ዕቀውቅና አገኘች፡፡

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስት ዶክተር ሂሩታ ካሳው ጉዳዩን አስመልከተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሮና ቫይረስን በመካለከል የቱሪዝም እንቅስቃሴዎችን ለማስጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል፡፡

ይህ ተከትሎም መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የዓለም አቀፍ የጉዞ እና ቱሪዝም ምክር ቤት ባስቀመጣቸው ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች መሰረት ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን በመካለከል የቱሪዝም እንቅስቃሴዎችን ማስጀመር እንደምትችል ዕውቅና መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

ይህም የቱሪዝም ዘርፉን ዳግም ለማነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል፡፡

የተሰጣት ማረጋገጫ ጎብኚዎች የደህንነት ስጋት ሳይገባቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ያደርጋለም ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

በአፍሪካ ይህ የደህንነት ማረጋገጫ የተሰጣቸው ሃገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 ናቸው፡፡

የደህንነት በማረጋገጫው በመስህብ ስፍራዎች ላይ ደህንነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች መገኘቱንም አስታውቀዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.