Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አጋርነታቸውን ለማጠናከር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ትብብርና አጋርነታቸውን ለማጠናከር መከሩ፡፡

በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተካሄደው የሁለትዮሽ ምክክር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ የኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት ሀገራችን በትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ እያደረገች ላለው የዕድገትና የለውጥ ተግባራት መሳካት እያበረከተ ላለው አስተዋፅዖ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በኮሪያ አለም ዓቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በኩልም ትብብርና አጋርነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በሁለቱ ወገኖች በኩል በሚደረጉ የአጋርነትና ትብብር ስራዎች በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የዲጂታል ክህሎት፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ሌሎች የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለማጠናከርና ወደተሻለ ደረጃ ለማደረስ እንደሚሰራ ገልጽዋል፡፡

የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ የኢትዮጽያ ተወካይ ዶንግ ሁ ኪም በበኩላቸው በሳይንሰና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተከናወኑ ላሉ ሁሉን አቀፍ የለውጥ ተግባራት ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽ በኤጀንሲው የሚተገበሩ ፕሮግራሞቹን ካለው የመንግስት የልማትና የለውጥ ተግባራት ጋር በማጣጣም እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በማሳያነትም በ8 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አመራርና የሰልጣኞች አቅም ለመገንባት በመከናወን ላይ ያሉ ተግባራትን የዘረዘሩ ሲሆን በቀጣይም በሁለቱ ወገኖች መካከል አዲስ ትብብርና አጋርነት መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.