Fana: At a Speed of Life!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱ ተነገረ፡፡
በምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል አንድ በኢቦላ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ቡቴምቦ በተባለው ከተማ አቅራቢያም አንዲት ሴት በቫይረሱ ሕይወቷ አልፏል ነው የተባለው፡፡
ይህን ተከትሎም ባለሥልጣናቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ አካባቢው እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ከሦስት ወር በፊት በምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል በሽታው ተከስቶ ነበር ፡፡
ኢቦላ ድንገተኛ እና አደገኛ የሆነ ትኩሳት፣ ድካም፣ የጡንቻ እና የጉሮሮ ሕመም የሚስከትል ቫይረስ ሲሆን በሽታው እየጠና ሲሄድ ማስመለስና ተቅማጥ ይጀምራል፡፡
ባስ ሲል ደግሞ የውስጥ እና የውጭ መድማትን ያስከትላል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.