125ኛውን የአደዋ በዓል በጋምቤላ ክልል ደረጃ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በጋምቤላ ክልል በመጪው ረቡዕ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታወቀ።
የበዓሉ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሎው ኡቡፕ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ በዓሉን ጀግኖች አባቶች የነበራቸውን አንድነት፣ አብሮነት፣ አይበገሬነትን በሚያወድስና በሚዘከር መልኩ ይከበራል።
በተለይም የአሁኑ ትውልድ የጀግኖች አባቶችን አኩሪ የሆነ ታሪካዊ ገድል ተገንዝቦ ያለበትን የዜግነት ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ የበዓሉ መከበር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በዓሉ በክልል ደረጃ በፓናል ውይይት፣ ስፖርትና ሥነ-ጹሁፍ ውድድር እንደሚከበር አስታውቀዋል።
ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስረድተዋል ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!