ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በየካቲት 12 ሆስፒታል ወረቀት አልባ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና የመረጃ ሲስተምን መረቁ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በየካቲት 12 ሆስፒታል ወረቀት አልባ የኤሌክትሮኒክ ዘመናዊ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና የመረጃ ሲስተምን መረቁ፡፡
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ብሎም በሃገሪቱ የመጀመሪያ የወረቀት አልባ የኤሌክትሮኒክ የጤና መረጃ ሲስተም ሲሆን፥ የህክምና አሰጣጥን በማዘማን የታካሚውን እንግልት ለመቀነስ እንደሚረዳ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የጤና ባለሙያውን ውጤታማነት በማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ጠቅሰው፥ አሰራሩ በሌሎች የከተማዋ ሆስፒታሎች እንደሚስፋፋም ገልጸዋል፡፡
የየካቲት 12 ሆስፒታል ሰራተኞች እና አመራሮች ለሰሩት ምሳሌነት ያለው ስራና በአገልግሎቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም ያለውን በማዘመን አዳዲስ ዘመናዊ ሆስፒታሎችን በመገንባት የከተማዋን የጤና ቱሪዝም መዳረሻነት ማረጋገጥ ይገባልም ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!